Explore All Propertie's Home Construction Mastery
4.8/5
Ratings from Customers
- About Us
Building a Brighter Future, Together Amibara Properties
Each All Properties development is designed with meticulous attention to detail, blending modern aesthetics with the pinnacle of comfort and convenience. From the moment you step into your new home, you’ll be captivated by the seamless integration of form and function, creating a living experience that exceeds your expectations. At the heart of our mission is a deep-rooted dedication to satisfying the evolving needs of our clients. We understand the importance of providing not just a house, but a home that truly reflects your lifestyle and aspirations. By consistently delivering exceptional quality and unparalleled value, we strive to make your dream of homeownership a reality.
The All Properties Advantages Amibara Properties
- Location
- Amenities
- View Matter
- Indoor Swimming Pool
- Indoor Fitness Center
- Our Amenities Amibara Properties
Gym
Spa
Meeting Hall
- Frequently Asked Questions
Everything You Need to Know About Our Services and Solutions Amibara Properties
አሚባራ ማለት አፋር ውስጥ የሚገኝ አንድ ወረዳ ሲሆን የስሙ ትርጉም የአጎት ልጅ ማለት ነው፡፡
አሚባራ ከተመስረተ 30 አመታትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን በስሩም በርካታ እህት ኩባንያዎች አሉት፡፡
አሚባራ እርሻ ልማት ኃ.የተ.የግ.ማ በ1986ዓ.ም የተመሰረተ፤ለበርካታ አመታት በጥጥ እርሻ ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን እስከ ዛሬ ከ17,000 ሄክታር በላይ ሲያሰተዳድር ቆይቷል፡፡
አሚባራ እርሻ ልማት በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ፣ በደቡብ ክልል በአርባ ምንጭ ከተማ፣ በወላይታ እንዲሁም በኦሞ ዞን የተለያዩ የእርሻ መሬቶችን በሊዝ ተከራይቶ ሲያለማ ቆይቷል።
ይህ ድርጅት በዋነኝነት የጥጥ እርሻ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ጎን ለጎን ግን የከሰል ምርትም ላይ ይሰራል፡፡በተጨማሪም ጥጥ መዳመጫ ማሽን ያለው ሲሆን የጥጡን ተረፈ ምርት ደግሞ ለከሰል ምርት ይጠቀማል ፡፡
አሚባራ እርሻ ልማት ኃ.የተ.የግ.ማ በተጨማሪም የከሰል ምርት ላይ የተሰማራ ሲሆን ይህ ድርጅት በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን በአመት እስከ 10,000 ቶን ለማምረት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ ድርጅት የሚጠቀመው ግብአት የጥጥ ተረፈ ምርት እና የሸንኮራ አገዳ ተረፈ ምርት ነው፡፡ ይህም የደን ጭፍጨፋን ይከላከላል፡፡ ሌላው ደግሞ ይህ የከሰል ምርት ከሌላው ለየት ሚያደርገው ለ6 ሰአታት መንደድ መቻሉ ነው፡፡
አሚባራ እርሻ ልማት ኃ.የተ.የግ.ማ 805 ቋሚ ስራተኞች እና 1,200 ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት፡፡
አሚባራ አቪዬሽን በ1999 ዓ.ም የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን በውስጡ 5 አውሮፕላኖችን ያስተዳድራል፡፡ እነዚህ አውሮፕላኖች የተለያዩ ጸረ ተባይ ኬሚካሎችን እስከ ምስራቅ አፍሪካ አገራት ድረስ በመሄድ የመርጨት እንዲሁም አንበጣን የመከላከል አገልግሎት ይሰጣሉ።
አሚባራ ትሬዲንግ በ2010 ዓ.ም የተመሰረተ አስመጪ እና ላኪ ድርጅት ሲሆን ጥሬ እና የተጣራ ጨው ማከፋፍል፣የታሸጉ ጁሶችን፣የህጻናት ዳይፐር፣የግብርና ኬሚካሎችን በማስመጣት እና በመላክ እንዲሁም የአርማታ ብረት በማስመጣት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው፡፡
ይህ ድርጅት በ1999 ዓ.ም 78 ሚሊዮን ብር ከመገዛቱም በተጨማሪ አንጋፋ እና ስመጥር ነው፡፡አዲስ ሞጆ የምግብ ዘይት ኮምፕሌክስ አ.ማ በዋነኝነት የኑግ፣የሱፍ፣የሶያ፣የጎመን ዘር እና የጥጥ ፍሬ ዘይት በማምረት ይታወቃል፡፡በስሩም 105 ቋሚ ሰራተኞች አሉ።
አዋሽ ብስኩት እና ዱቄት ፋብሪካ በ1998 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን ይህ ፋብሪካ በቀን እስከ 78 ኩንታል ዱቄት የሚያመርት ድርጅት ነው፡፡
በ 1996 ዓ.ም የተመሰረተው አሚባራ ትራንስፖርት ድርጅት በስሩ ወደ 30 የሚሆኑ የጭነት ተሳቢ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን ወደተለያሩ የሃገሪቱ ክፍሎች በመጓጓዝ የጭነት አገልግሎት ይሰጣል።
አሚባራ ፕሮፐርቲስ በ2014 ዓ.ም የተመሰረተ የቤት አልሚ (Property Developer) ድርጅት ሲሆን አሁን ላይ ፍል ወሃ አካባቢ ከወዳጅነት ፓርክ አጠገብ 35,751ካ.ሜ ላይ ያረፈ ግዙፍ ፕሮጀክት እየሰራ ይገኛል፡፡ አሚባራ ፕሮፐርቲስ አላማው የተሻለ የኑሮ ዘይቤ (A Better Life Style) መፍጠር ነው ፡፡
በተጨማሪም ይህ ግዙፍ ድርጅት በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ መካከል በአራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ጎጃም በረንዳ አካባቢ 32 ችግረኛ አባውራዎችን የሚይዝ G3 የሆነ የመኖሪያ ስፍራ ስርቶ ለማስረከብ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡ ይህ የመኖሪያ ስፍራ 24 ባለ1 መኝታ እና 8 ባለ2 መኝታ የሚካትተ ይሆናል፡፡
አሚባራ ፕሮፐርቲስ አሁን ላይ በፍል ውሃ አካባቢ ከወዳጅነት ፓርክ አጠገብ በ 35,751 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር እየገነባ ነው።
ከዲዛይን ጀምሮ የኮንስትራክሽን ሂደቱ የሚከናወነው ከዱባይ፣ ከቱርክ፣ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ከቻይና ከተወጣጡ እውቅ ድርጅቶችና ባለሙያዎች ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ዘመናዊ የኑሮ ዘይቤ የሚለውን አባባል አዲስ ትርጉም የሚሰጥ፤በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ፕሮጀክቶች በውበት እና በጥራት ቀዳሚ የሆነ የመኖሪያ መንደር እንደሚሆን ይታመናል።
የግንባታ ሒደቱ አሁን ላይ የህንጻ A 50 በመቶ ተጠናቁል ፡፡ የህንጻ B ደግሞ የመሠረት ስራውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
‘A’ እና ‘B’ ህንጻዎች በ21 ወር ውስጥ ግንባታቸው አልቆ ለድንበኞች የሚረከቡ ሲሆን ጠቅላላ ፕሮጀክቱ ደግሞ በ66 ወር ውስጥ ይጠናቀቃል።
በመሀል ከተማ ፍል ዉሃ አካባቢ በወዳጅነት ፓርክ ማራኪ እይታ እንዲሁም በአዲስ አበባ ግዙፍ ህንጻዎች እይታ የተከበበው የአሚባራ ፕሮፐርቲስ የመኖሪያ መንደር፤ ከቤተ-መንግስት፣ከሊሴ ገብረ ማርያም፣ከሳይንስ ሙዚየም፣ከሸራተን፣ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም ከተለያዩ ዋና ዋና መንገዶች በቅርብ ርቀት መገኘቱ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡
የአሚባራ ፕሮፐርቲስ የመኖሪያ መንደር እያንዳንዱ ህንጻዎች ሲገነቡ የውሀ ስርገትን የሚከላከል ምድር ቤት (Water Proof Basement) እንዲሁም እሳት አደጋ ቢያጋጥም ከአንዱ ወለል ወደ ሌላኛው ወለል እንዳይሄድ የሚያደርግ በር (Air Pressured Door) በደረጃ መወጣጫው ላይ የተገጠመለት ነዉ፡፡ በተጨማሪም ‘A’ እና ‘B’ ህንጻ መካከል 21 ሜትር ርቀት አለው። ህንጻዎቹ የተገነቡት ፍላት ስላብ(Flat Slab) ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሲሆን የተፈጥሮ ብርሃን በቀላሉ ወደ ቤቶቹ እንዲገባ ያስችላል።
የአሚባራ ፕሮፐርቲስ የመኖሪያ መንደር በውስጡ መናፈሻ ስፍራ፣ ፉትሳል(Futsal) የቴኒስ እና የቅርጫት ኳስ መጫወቻ(Tennis and basketball court) ፣ የበረዶ ላይ መንሸራተቻ (Indoor ice skating arena)፣ የስፖርት ጂምናዚየም እና ስፓ፣ 2 የመዋኛ ገንዳዎች ፣ሲኒማ፣ ኢንተርኮም ፣መጠባበቂያ ጄኔሬተር፣ የደህንነት ካሜራዎች፣ የቆሻሻ ማስወገጃ (Garbage Chute)፣ የኤሌክትሪክ መኪና ሃይል መሙያ ጣቢያ(electric charging station) ፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ የሚያካትት ሲሆን በአንድ ህንጻ ላይ 2 ሰፋፊ ለድንገተኛ ጊዜ ስትሬቸር ማስገባት የሚችሉ አሳንሰሮች ይዟል። 3.7 ሜትር ከፍታ ያለው ምድር ቤት አምቡላንስ የሚያስገባ በመሆኑ ህመምተኞችን ከአሳንሰሩ በመቀበል ማጓጓዝ እንዲችል እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ ቢፈጠር የእሳት አደጋ ምድር ቤት(Basement) ድረስ በመግባት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው።
በተጨማሪም ለመተላለፍ ሰፊ ስፋት ያለው በቂ የመኪና ማቆሚያ ከተለያዩ መግቢያ እና መውጫ በሮች ጋር ምድር ቤቱ ይዟል።
ህንጻዎቹ የተገነቡት ፍላት ስላብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስለሆነ የተፈጥሮ ብርሃን በቀላሉ ወደ ቤቶቹ እንዲገባ ያስችላል። በተጨማሪም እያንዳንዱ ቤት 3.70 ሜትር ከፍታ ስላለው የተፈጥሮ አየር ዝውውር (Ventilation) እንዲኖረዉ ያግዛል።
አሚባራ ፕሮፐርቲስ አሁን ለሽያጭ ያወጣቸዉ 2 ሕንጻዎች (A እና B) G+17 ሲሆኑ በዉስጣቸዉ ባለ አንድ መኝታ ፣ ባለ ሁለት መኝታ ፣ ባለ ሶስት መኝታ፣ ባለ አራት መኝታ እና ፔንት ሃውስ የቤት አማራጮችን ይዘው በወለል 8 አባወራ የሚያሰፍሩ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ህንጻ 3 ምድር ቤት (Basement) አለዉ፡፡
ባለ አንድ መኝታ= 86 ካ.ሜ እና 91ካ.ሜ
ባለ ሁለት መኝታ= 135ካ.ሜ ፣ 142ካ.ሜ እና 163ካ.ሜ
ባለ ሶስት መኝታ= 172ካ.ሜ፣ 178ካ.ሜ፣ 180ካ.ሜ እና 187ካ.ሜ
ባለ አራት መኝታ= 211ካ.ሜ፣ 221ካ.ሜ እና 267ካ.ሜ
ፔንት ሃውስ= 424ካ.ሜ እና 494ካ.ሜ(ፍላት)፣ 646ካ.ሜ እና 662ካ.ሜ (ዱፕሌክስ)
የአሚባራ ፕሮፐርቲስ የመኖሪያ መንደር በአጠቃላይ 9 ህንጻዎች ያሉት ሲሆን በውስጡም 7 የአፓርታማ ህንጻዎችን፣ 1 የሆቴል አፓርታማ ህንጻ፣ 1 ግዙፍ የቢሮ ታወር፣ 11,000 ካሬ ላይ ያረፈ G 3 ግዙፍ የገበያ ማዕከል እንዲሁም 1 የጋራ መገልገያ ህንጻ (Communal Space) በቀጣይነት ይገነባል።
የጋራ መገልገያ ህንጻ ፉትሳል፣ የቅርጫት ኳስና የቴኒስ መጫወቻ፣ 2 የመዋኛ ገንዳዎች፣ የስፖርት ጂምናዚየም እና ስፓ እንዲሁም ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚያገለግል ትልቅ አዳራሽ ያካትታል።
ዋጋችን በኢንደስትሪው ካሉ አልሚዎች አንጸር ሲታይ በጣም ጥሩ የሚባል እና ከቤቱ ጋር የተመጣጠነ ነው፡፡ ይህም ከሌሎች አልሚዎች እንድንመረጥ ከሚያደርገን ብዙ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ የካሬ ዋጋ በተመለከተ በካሬ ከ $2500 እስከ $2800 ድረስ አማራጮች አሉ፡፡
ቅድመ ክፍያ 10% ሲሆን ደንበኞች 5% በመክፈል በMOU በመስተናገድ ከ1 ወር በኋላ ቀሪውን 5% ክፍያቸውን እነዲያጠናቅቁ አሚባራ ፕሮፐርቲስ ለደንበኞቹ አማራጭ አቅርቧል።
አሁን ላይ ለሽያጭ የወጡ ህንጻዎች A እና B ናቸው፡፡ ሆኖም የአከፋፍል ሂደታቸው ግን ይለያያል ፡፡የህንጻ ‘A’ አከፋፍል በጊዜ ገደብ (Time Based) ሲሆን የህንጻ B ደግሞ ግንባታው በድረስበት ደረጃ (Progress Based) ይሆናል ፡፡ ደንበኞች ቅድመ ክፍያ ከከፈሉ በኋላ ቀሪውን በ 6 ዙር በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው የሚያጠናቅቁ ይሆናል።
የአሚባራ ፕሮፐርቲስ የግንባታ ሳይት የሚገኝበት አካባቢ ለኑሮ ምቹ ከመሆኑም ከተለያዩ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ተቋማት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቅርብ ርቀት ላይ መገኘቱ ተመራጭ ያደርገዋል።
በአካባቢው ያለው ውብ እይታ መንፈስን የሚያድስ፣ ነፋሻማ ንጹህ አየር ያለው፣ የዘመነ ኑሮን የሚኖሩበት ልዩ ስፍራ ነው።
ለግል ቢኖሩበት፣ ቢሸጡት ወይም ቢያከራዩት የሚያተርፉበት ጥሩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው።
በረዥም ጊዜ ክፍያ መፈጸም ይቻላል?
አሁን ባለው ተጨባጭ የባንክ አሰራር ሒደት ባንኮች ብድር ለመስጠት የቤት ካርታ ፕላን ይፈልጋሉ፤ የሚመለከተው የመሬት አስተዳደር ካርታ አሰራር ሒደት የሚከናወነው ደግሞ የቤቱ ግንባታ 70 በመቶ ወይም ጣራ ከደረሰ በኋላ መሆኑ በቅድሚያ ብድሩን ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን በእዚህ ሁኔታ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከእዚህ በተሻለ መስራት እንዳለብን እናምናለን፡፡ የተጀመሩ ሁኔታዎችም አሉ፡፡
አሁን ባለው የአገሪቷ ሕግ መሰረት አንድ ሰው ንብረት ሊኖረው የሚያስችልው አግባብ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆነ፣ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆነ፣ በጋብቻ ኢትዮጵያዊ ከሆነ እና የኢንቨስትመንት ፍቃድ ካለው ነው፡
Hi, I wanted to know your price.
Please contact us +251967034405
I accept this leave request to join my dear friend and and I hope you accept this request as soon as possible.
I am intersted